Fana: At a Speed of Life!

የመከላከያ ሰራዊት የኢትዮጵያ አንድነት ውል የተቋጠረበት ነው-የጎንደር ከተማ ከንቲባ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ከአንድ ቤተሰብ አንድ ዘማች ” በሚል መሪ ቃል የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከከተማው ህዝብ ጋር ምክክር አካሄደ
ደህንነት ሳይረጋገጥ እንደ ሀገር መቀጠል አይቻልም ያሉት የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ሞላ መልካሙ ፥የመከላከያ ሰራዊት የኢትዮጵያ አንድነት ውል የተቋጠረበት በመሆኑ ውሉን ማጥበቅ አለብን ብለዋል።
ሰራዊቱን በሞራል በስንቅነና በትጥቅ መደገፍ ያስፈልጋል ያሉት ከንቲባው፥ ኢትዮጵያ አስተማማኝ ሀገር ሆና በምስራቅ አፍሪካ የተከበረች እንድትሆን የመከላከያ ሰራዊቱ መጠናከር አለበትም ሲሉ ተናግረዋል።
መከላከያ ሰራዊቱን ተቀላቅለን ካላጠናከርን በትንሹም በትልቁም መጠቃት እንጀምራለን ያሉት አቶ ሞላ፥ ወጣቶች መከላከያ ሰራዊቱን መቀላቀል አለባቸው ሲሉም አሳስበዋል።
የሰ/ምዕ/ግንባር ሎጂስቲክስ አስተባባሪው ኮሎኔል ዘዉዱ ስሜነህ በበኩላቸው ፥የመከላከያ ሰራዊት የኔ የሚለው ሀብቱ ሀገሩ ብቻ ናት ፣ ሀገር እንድትኖር በጋራ ልንተባበርና ጠንካራ ሰራዊት መፍጠር ይገባል ብለዋል።
ህዝቡ አሁን ላይ ለሰራዊቱ እያሳየ ያለው ድጋፍ የሚደነቅ ነው ያሉት ኮሎኔሉ፥ ከዚህ በተጨማሪም የሰራዊቱ አባል በመሆን የድርሻን መወጣት ይገባል ብለዋል።
የጎንደር ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት የአደረጃጀት ሀላፊ አቶ ግርማይ ልጃለም ለውይይት መነሻ ባቀረቡት ፅሁፍ፥ ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ የሚከፈለው ወታደር ሳይኖራት በሀገር ወዳድ ጀግኖቿ ራሷን አስከብራ ኖራለች ብለዋል።
አሁንም ወጣቱ ሰራዊቱን ተቀላቅሎ የውስጥና የውጭ ጠላቶችን ሊመክት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
የውይይቱ ተሳታፊ ወላጆችም ልጆቻቸውን ለዘመቻ እየላኩ መሆኑን ተናግረው፥ ወጣቱ ለሀገሩ ህልውናና ለመብቱ መከበር ሲል ሰራዊቱን ሊቀላቀል ይገባል ብለዋል።
ወጣቶችም ለሀገራቸውና ለቤተሰቦቻቸው ሲሉ ሰልጥነው አለኝታ ለመሆን ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በሙሉጌታ ደሴ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.