Fana: At a Speed of Life!

በቴክኖሎጂ ዘርፍ ሀገራዊ ለውጥ ለማምጣት ትብብርና ቅንጅት ወሳኝ ነው -ዶ/ር አህመዲን መሐመድ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በተጠሪ ተቋሙ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት ስር የነበረውን ህንፃ ለመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ማስረከቡን አስታወቀ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አህመዲን መሐመድ፣ የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል አህመድ ሃምዛ፣ የቴክኖሎጂና የኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሙሉቀን ቀሬ እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሳንዶካን ደበበ በእርክክቡ ወቅት በዘርፉ በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

እንደ መከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ያሉ ተቋማት ለቴክኖሎጂ እድገት ትልቅ አስተዋፅኦ ስላላቸው በዘርፉ ሀገራዊ ለውጥ ለማምጣት በጋራና በትብብር መስራት ወሳኝ መሆኑን ዶክተር አህመዲን ተናግረዋል።

የሀገሪቱን የሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ከግብ ለማድረስና ሀገራዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ በዘርፉ የሚሰሩ ተቋማትን ችግር መቅረፍ እንደሚገባ የተናገሩት ሚኒስትር ዴኤታው÷ የአዲሱ ህንፃ ርክክብም የዚህ አንዱ አካል ነው ብለዋል።

የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ለዋና መስሪያቤት የሚሆን የቢሮ ህንፃ ስላልነበረው ስራዎችን በሙሉ አቅም ለመስራት ሲቸገር መቆየቱም ተገልጿል፡፡

አዲሱ ህንፃ የተሟላ መሰረተ ልማት የተዘረጋለት በመሆኑ ለተቋሙ ተልዕኮ ስኬት ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎ እደሚታመንበት ከኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+3
53
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.