Fana: At a Speed of Life!

ለአሸባሪዎች ድጋፍ በማድረግ ወንጀል በተጠረጠሩ 15 ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሰረተ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል ለአሸባሪዎቹ ህወሓት እና ሸኔ ድጋፍ በማድረግ ወንጀል በተጠረጠሩ 15 ግለሰቦች ላይ ክስ መመስረቱን የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ።

የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዋና አቃቤ ህግ አቶ አዩብ አህመድ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጁትን ህወሓት እና ሸኔን በክልሉ የሚደግፉ ግለሰቦችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከህብረተሰቡ እና ጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው።

በዚህም በክልሉ ለአሸባሪዎቹ የፋይናንስ ድጋፍ የሚያደርጉ እና ለጥፋት የሚያነሳሱ ግለሰቦች እና ድርጅቶችን በመቆጣጠር የምርመራ እና ጉዳያቸው በህግ እንዲታይ ክስ የመመስረት ስራ እየተካሄደ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

አሁን ላይ ሽብርተኞችን በመደገፍ እና የሽብር ወንጀል በመፈጸም ወንጀል በተጠረጠሩ 15 ግለሰቦች ላይ ክስ እንደተመሰረተ ነው አቶ አዩብ ያስታወቁት።

በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው ተጠርቶ ከወንጀሉ ነፃ ሆነው የተለቀቁ ግለሰቦች እንዳሉም አመላክተዋል።

እንዲሁም ሰባት ድርጅቶች ታሽገው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ጠቁመው፤ ባለንብረቶቹ ለጊዜው ቢሰወሩም 11 ተሽከርካሪዎቻቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጠቅሰዋል።

በቀጣይም ሽብርተኞችን በማንኛውም መልኩ በመደገፍ የሀገርን ሰላም ለመንሳት የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች እና ድርጅቶችን ተከታትሎ ለህግ የማቅረብ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.