Fana: At a Speed of Life!

ባለሃብቶች ትርፋቸውን ብቻ ከማሰብ ይልቅ ሃገርን ማዳን ይገባቸዋል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)አሁን ያለንበት ወቅት አስከፊ እና ፈተና የበዛበት በመሆኑ በተለይ የኢትዮጵያ ባለሃብቶች ትርፋቸውን ብቻ ከማሰብ ይልቅ ሃገርን ማዳን ይገባቸዋል ሲሉ አቶ መላኩ አለበል አሳሰቡ፡፡

አሸባሪው እና ዘራፊው ቡድን ስልጣን ላይ በቆየባቸው 27 ዓመታት በርካታ የኢኮኖሚ አሻጥሮችን ሲሰራ እንደነበር የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ገልጸዋል፡፡

በነጻ ኢኮኖሚ ሥርዓት ሽፋን አንድን አካል ብቻ ተጠቃሚ የሚያደርግ ፖሊሲ ማውጣት፣ የመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካን ብቻ ተጠቃሚ ለማድረግ ተጨማሪ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች እንዳይገነቡ የሚያግድ ፖሊሲ ማውጣት፣ ለኮንስትራከሽን የሚውሉ ግብዓቶችን በውስንና ለአሸባሪው ቡድን ታማኝ በሆኑ አካላት ብቻ ከውጪ እንዲመጡ መፍቀድ፣ በኢንቨስመንት ሽፋን ሰፋፊ መሬቶችን በመያዝ ከባንኮች የብድር አገልግሎት መጠየቅ እና ብድሩን በተገቢ ዲሲፒሊን አለመመለስ ከተሰሩ አሻጥሮች ውስጥ ጠቅሰዋል፡፡

ይህንን የኢኮኖሚ አሻጥር የተረዳው የለውጡ ሃይል ከለውጡ እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ እንቅስቃሴ እያደረገ ባለበት ወቅት ይህ ጽንፈኛ በኢትዮጵያ ላይ በከፈተው ጦርነት የተፈለገው ውጤት እንዳልመጣ አቶ መላኩ አያይዘው ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ይህንን የኢኮኖሚ አሻጥር ለመቀልበስ እና በኢትዮጵያ ላይ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ እንዳይፈጠር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው ባለሃብቶች ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

አሁን ያለንበት ወቅት አስከፊ እና ፈተና የበዛበት በመሆኑ በተለይ የኢትዮጵያ ባለሃብቶች የትርፍ ህዳጋቸውን ከማሰብ ይልቅ ሃገርን ወደ ማዳን እንድምታ መሸጋገር እንደሚገባቸው ማሳሰባቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.