Fana: At a Speed of Life!

“የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት” ንቅናቄ በጎንደር ከተማ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት” ንቅናቄ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር በጎንደር ፋሲለደስ ቤተ መንግሥት ተካሄደ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ባለስልጣናት በተገኙበትም ደብዳቤ የመላክ መርሃ ግብሩ በይፋ መጀመሩ ተገልጿል፡፡

 

የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ሞላ መልካሙ ÷ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በከፈተው ጦርነት የደረሰውን ቀውስ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስገንዘብ ይህ የነጭ ደብዳቤ ማዕብል ትክክለኛ የሆነውን እውነታ ያስረዳል ብለዋል።

የሽብርተኛው ቡድን የፈፀመውን ጭፍጨፋ እና በንፁሃን ላይ የፈፀመውን ዘግናኝ ድርጊት ለቀረው አለም ለማስረዳት አዋጭ የዲፕሎማስ መንገድ መከተል ይገባል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በሚላከው ነጭ ፖስታም በከተማው 65 ሺህ ወጣቶች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በምናለ አየነው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.