Fana: At a Speed of Life!

የሞጆ – ባቱ የመንገድ ፕሮጀክት መስከረም 10 አገልግሎት ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሞጆ – ባቱ የክፍያ መንገድ ፕሮጀክት መስከረም 10 አገልግሎት እንደሚጀምር የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ካሳሁን ጎፌ ገለጹ፡፡

ሚኒስትር ዴኤታ ካሳሁን ባደረጉት የመስክ ምልከታ 92 ኪ.ሜ የሚሸፍነው የሞጆ – ባቱን የክፍያ መንገድ ስራ ለማስጀመር አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቃቸውና አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ዋና ዋና ግብዓቶች መሟላታቸውን ገልጸዋል፡፡

በዚህም ከመስከረም 10/2014 ጀምሮ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ሚያዝያ 2013 ዓም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተመረቀው የሞጆ- ሀዋሳ የመንገድ ፕሮጀክት አካል የሆነው የሞጆ ባቱ የክፍያ ፍጥነት መንገድ የተሟላ የክፍያ ማከናወኛ ስርዓት ተሟልቶለት መስከረም 10/2014 ዓም ለአገልግሎት ክፍት መሆኑ ትልቅ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፈይዳ እንዳለው አቶ ካሳሁን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙስጠፋ አባሲመል÷ 92 ኪ.ሜ የሚሸፍነው የሞጆ – ባቱን የክፍያ መንገድ ስራ ለማስጀመር የመክፈያ ማሽኖች ተከላ፣ የታሪፍ ዝግጅት፣ የሠራተኞች ቅጥርና ስልጠና፣ የተለያዩ ግብዓቶችን የማሟላት፣ አስተዳደራዊ ስራዎች መሰራቱ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ከአከባቢው ማህረሰብና ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በቅንጅት ለመስራት በየደረጃው ውይይት ተካሂዷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.