Fana: At a Speed of Life!

”ካለኝ ቀንሼ ለመከታዬ”

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ”ካለኝ ቀንሼ ለመከታዬ” በሚል መሪ ሃሳብ ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ፡፡

የቀድሞ የጦር ጉዳተኞች፣ የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋውያን ተሃድሶ እና የማህበራዊ ችግር ተጎጂዎች ልማት ማዕከላት ለመከላከያ ሰራዊት ከግማሽ ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል።

የቀድሞ የጦር ጉዳተኛ መቶ አለቃ ጥላየ ሽፈራው ለኢዜአ  እንደተናገሩት ማዕከላቸው ከጉዳተኞቹ የእንቁላል፣ ወተት

እና የስጋ ወጫቸው ላይ ቀንሰው 289 ሺህ 741 ብር ድጋፍ አድርጓል።

ለኢትዮጵያ ህልውና እየተፋለመ ለሚገኘው ጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ በማድርጋቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያውያን ሁሉ ለመከላከያ ሰራዊት የሚያደርጉትን ድጋፍና እገዛ አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ነው ያሉት ።

በተመሳሳይ የአረጋውያን ተሃድሶ ልማት ማዕከልና የማህበራዊ ችግር ተጎጂዎች ማህበር በጋራ በመሆን 263 ሺህ 715 ብር ድጋፍ አድርገዋል።

የአዲስ አበባ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮም  ለሰራዊቱ የ20 ሚሊየን ብር ነው ድጋፍ ያደረገው።

የቢሮው ሃላፊ አቶ ተፈራ ሞላ፥ ከገንዘብ ድጋፉ በተጨማሪ የተቋሙ ሰራተኞች ደማቸውንም ለግሰዋል ብለዋል።

በቀጣይ ቢሮውና በስሩ ያሉት ተቋማት የመከላከያ ሰራዊቱንና በጦርነት ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን  ለመደገፍ የሚያደርጉትን እገዛ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ እንደተናገሩት ኢትዮጵያን ከውጭ ጠላት ጠብቆ ያቆያትን የመከላከያ ሰራዊት በመውጋት ክህደት የፈጸመውን ሃይል ለመደምሰስና ኢትዮጵያን ለማሻገር ጊዜው አሁን ነው።

ጦርነት ውድመትን የሚያመጣ ቢሆንም ሁሉም ኢትዮጵያዊ አንድ ሆኖ አገሩን እንዲጠብቅ ጦርነቱ እድል ፈጥሮልናል ብለዋል።

አገር አፈርሳለሁ ብሎ የተነሳውን የህወሓት አሸባሪ ቡድን መከላከያው፣ ሚሊሻው፣ አርሶአደሩና ወጣቱ በግንባር በመሰለፍ እየተፋለሙ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የተደረገውን ድጋፍ የተረከቡት የመከላከያ ሚኒስቴር ተወካይ ኮሎኔል ተስፋዬ መኮንን፤ ለሁሉም ምስጋና አቅርበዋል።

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.