Fana: At a Speed of Life!

በአጣዬ ለወደሙ ቤቶች መልሶ ግንባታ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአጣዬ ከተማ አስተዳደር የወደሙ ቤቶችን መልሶ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ይፋት ልማት ማኅበር የ10 ቤቶችን ግንባታ አስጀመረ።

ይፋት የልማት ማኅበር በአጣዬ፣ ኤፍራታና ግድም ወረዳ ሁለት መቶ ቤቶችን ለመገንባት አቅዶ ወደ ተግባር መግባቱ ነው የተገለጸው።

የልማት ማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ክፍሉ ቢፈሩ ÷ ማህበሩ አንድ መቶ ሚሊየን ብር መድቦ ቤቶችን የመገንባት ሥራ ጀምሯል ብለዋል።

ዛሬ ግንባታቸው የተጀመረው 10 ቤቶችም በ9 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር እንደሚገነቡ ተገልጾ ግንባታቸው በ5 ወራት እንደሚጠናቀቅ ዕቅድ ተይዟል።

የዞኑ ከተማ ልማትና ቤቶች ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ በድሉ ውብሸት በበኩላቸው÷ የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ከ1 ሺህ 400 በላይ በቀጣናው የወደሙ መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት እየተንቀሳቀሰ ነው ብለዋል፡፡

በአካባቢው የደረሰውን ውድመት መልሶ ለማቋቋም ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ ያቀረቡት የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አገኘሁ መክቴ ሲሆኑ፥ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም እየተሠራ መሆኑንም ተናግረዋል።

በቀጣይም ሆቴሎችና ሌሎች የአገልግሎት ተቋማትን ለመገንባት መታቀዱን ከአሚኮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.