ለሃገር ህልውና በጋራ በመቆም የጁንታውን አላማ ለማክሸፍ ዝግጁ ነን – ወጣቶች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ለሃገር ህልውና በጋራ በመቆም የአሸባሪውን ቡድን አላማ ለማክሸፍ ዝግጁ ነን አሉ በደሴ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ ስልጠናቸውን የጨረሱ ወጣቶች።
ወጣቶቹ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬት እንደተናገሩት÷ አካባቢያቸውን እና ሃገራቸውን ለመጠበቅ የሚያስችል መሠረታዊ የውትድርና ስልጠና መውሰዳቸውን ገልጸዋል።
ጁንታው ያደረሠው ጥፋት አሰቃቂ ነው ያሉት ወጣቶቹ÷ ከሌሎች የጸጥታ ሀይሎች ጋር በመቀናጀትና ግንባር ድረስ በመሰለፍ መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን ብለዋል።
የአራዳ ክፍለ ከተማ የህዝብ ሰላምና ደህንነት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ መስፍን አራጌ በበኩላቸው÷ ወጣቱ እያሳየ ያለው ተነሳሽነት ኢትዮጵያ ሁሌም ደጀን እንዳላት ማሳያ እንደሆነ ነው የጠቆሙት።
ወጣቱም የሃገር መከላከያ ስራዊቱን በመቀላቀል የህልውና ዘመቻውን ሊደግፍ እንዲገባ ገልጸዋል።
በከድር መሀመድ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!