Fana: At a Speed of Life!

የደሴ ከተማ የንግዱ ማህበረሰብ ለጸጥታ ሀይሉ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደሴ ከተማ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት በደላንታ ግንምባር ለሚገኘው የሀገር መከላከያ እና ለአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ ድጋፍ አድርገዋል።
ግንምባር ድረስ በመገኘት ድጋፉን ያደረጉት ነዋሪዎቹ፥ ለሀገር ህልውና ጁንታውን በመደምሰስ እየተዋደቀ ላለው የሀገር መከላከያ እንዲሁም የአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ ድጋፍ ማድረጋችን ከዜግነት ግዴታችን ቢያንስ ጥቂቱን እንዳደረግን እንዲሰማን አድርጓል ብለዋል።
ሀገር ስትኖር ነው ሰርተን መለወጥ የምንችለው ያሉት ነዋሪዎቹ፥ ጁንታው የከፈተብን ጦርነት በቁርጥ ቀን ልጆቻችን የሀገር መከላከያ እና የአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ ይቀለበሳል ነው ያሉት።
እኛም ለሰራዊቱ ደጀን መሆናችንንም ማሳየታችንን እንቀጥላለን ካስፈለገም ለመዝመት ዝግጁ ነን ሲሉ ተናግረዋል።
በደላንታ ግንምባር ሰራዊቱን ምሳ የማብላት መርሃግብር የተካሄደ ሲሆን፥ድጋፉ የቁሳቁስ ድጋፍንም ያጠቃለለ መሆኑ ተመላክቷል።
በስነስርአቱ ላይ የመከላከያ ከፍተኛ አመራሮች የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሰይድ መሀመድን ጨምሮ ሌሎች የስራ ሃላፊዎችም ተገኝተዋል።
በሀብታሙ ተ/ስላሴና ኢሳያስ ገላው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.