Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በባህርዳር ጊዜያዊ ማቆያ የሚገኙ ዜጎችን ጎብኝተዋል

 

አዲስ አበባ ፣መስከረም 6፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በአማራ ክልል ጁንታው ባደረሰው ጥቃት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በባህርዳር ጊዜያዊ ማቆያ የሚገኙ ወገኖችን ጎብኝተዋል።

ሚኒስትሯ በአማራ እና አፋር ክልሎች ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች እርዳታ በአፋጣኝ ለማዳረስ እና የመልሶ ለማቋቋም ፈጣን ምለሽ ለመስጠት ከፍተኛ ስራ ተጠናክሮ መሰራቱ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

ለዚህም ስራ ይረዳ ዘንድ ከተባበሩት መንግስታት እና ሌሎች አለም አቀፍ ሰብአዊ ድርጅቶች ጋር በቅርበት እንደሚሰራ ሚኒስትሯ አስረድተዋል።

ላለፉት ዘጠኝ ቀናት በዋግ ኽምራ ዞን የእርዳታ ጭነት የጫኑ መኪናዎች በጥፋት ሃይሉ ምክንያት እንቅስቃሴያቸው ተስተጓጉሎ የነበረ ቢሆንም አሁን ችግሩ እንደተፈታ ተናግረዋል።

እስካሁን ድረስ የጥፋት ሃይሉ በተለያዩ አካባቢዎች ባደረሰው ጥቃት ምክንያት ከ500 ሺህ በላይ ወገኖች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን ከሰላም ሚንስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.