Fana: At a Speed of Life!

“የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት” የትዊተር ዘመቻና የማህደር ምስል ዛሬ ይቀየራል

አዲስ አበባ ፣መስከረም 7፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ)”የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት” የትዊተር ዘመቻና የማህደር ምስል ዛሬ ከቀኑ 7፡00 ሠዓት ከ7 ደቂቃ ላይ የመቀየር መርሃ ግብር እንደሚካሄድ የዘመቻው ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አስታወቀ።

የማኅበራዊ ትስስር ገጾች ተጠቃሚ ኢትዮጵያዊያን በተጠቀሰው ሠዓት የማህደር ምስላቸውን /ፕሮፋይል ፒክቸር/ የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት በሚል በተዘጋጀው እንዲቀይሩም ጥሪ ቀርቧል።

በተጨማሪም የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት ዘመቻ ዓላማዎችን መሰረት ያደረገ የትዊተር ዘመቻ እንደሚካሄድና ለዘመቻው የሚሆኑ አቢይ ርዕሶች /ሀሽታጎች/ መዘጋጀታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የኢትዮጵያን እውነታ ማስረዳትና የህወሓት ቡድን እየፈጸማቸው ያሉ እኩይ ተግባራትን ማጋለጥን ዓላማ ያደረገው “የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት” ዘመቻ መስከረም 3 ቀን 2014 ዓ.ም ነው የተጀመረው።

በዘመቻው የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉበትም ይገኛሉ።

“የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት” የተጻፉ ደብዳቤዎች የፖስታና የተለያዩ እቃዎችን በዲኤችኤል አማካኝነት ወደ ዋይት ሐውስ እንደሚላኩ የብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ አቶ አክሊሉ ታደሰ ጠቁመዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.