Fana: At a Speed of Life!

የነጩ ፖስታ ለነጩ ቤተመንግስት ዘመቻ በሽብርተኛው ህወሓት ከትምህርት ገበታቸው ውጪ የሆኑ ተማሪዎችን ይወክላል- ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ

አዲስ አበባ ፣መስከረም 7፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች የኢትዮጵያን እውነታ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማሳወቅ የተጀመረውን “ነጩ ፖስታ ለነጩ ቤተመንግስት” ዘመቻን ፊርማቸውን በማኖር አስጀምረዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ÷የህወሓት የሽብር ቡድን ከ10ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች ላይ ጉዳት በማድረስ ከ3ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ውጪ እንዲሆኑ አድርጓል ብለዋል።

በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክንያት በአማራ ክልል 1 ነጥብ 5 ሚሊየን፣ በትግራይ ክልል ከ1 ነጥብ 4 ሚሊየን፣ በአፋር ክልል ደግሞ 200ሺህ በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ውጪ ሆነዋል ያሉት ሚኒስትሩ÷ ይህንን እውነት የአሜሪካው ፕሬዝዳንትና ካቢኔያቸው እንዲያውቁትና ቡድኑን ተጠያቂ እንዲያደርጉት እንፈልጋለን ብለዋል።

የህወሓት የሽብር ቡድን እስከ አሁን በትግራይ 6 ሺህ፣ በአማራ 3 ሺህ፣ በአፋር ደግሞ 500 ትምህርት ቤቶችን ከጥቅም ውጭ ማድረጉን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.