Fana: At a Speed of Life!

ሆስፒታሉ የ160 ሚሊየን ብር ውድመት ደርሶበታል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በንፋስ መውጫ ሆስፒታል የ160 ሚሊየን ብር ውድመት ማድረሱን የንፋስ መውጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ብርሃን ሙሉ ገለፁ፡፡
የሆስፒታሉ የህክምና እቃዎች፣ የላቦራቶሪ ማሽኖች፣ መድሀኒቶች እና የተለያዩ መገልገያ መሳሪያዎች ወድመዋል ብለዋል ሥራ አስኪያጁ፡፡
ሆስፒታሉ በደረሰበት ጉዳትም ለአካባቢው ማህበረሰብ ሙሉ አገልግሎት እየሰጠ አለመሆኑን አስታውቀዋል።
መጠነኛ ድጋፍ እየቀረበ መሆኑን ጠቁመው የተደረገው ድጋፍ ግን መደበኛ አገልግሎት ለመስጠት የሚያበቃ አለመሆኑን ለፕሬስ ተናግረዋል፡፡
ሆስፒታሉ በሙሉ አቅሙ ላህብረተሰቡ አገልግሎት ለመስጠት እዲችል÷ ተጨማሪ የህክምና እቃዎችና የመድሃኒት አቅርቦት ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.