Fana: At a Speed of Life!

የህወሓትን ሀገር የማፍረስ ሴራ ቅዥት ነው – ዘማች ወጣቶች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገራቸውን በወታደርነት በማገልገል የአሸባሪው ህወሓትን ሀገር የማፍረስ ሴራ ቅዥት ለማድረግ መዘጋጀታቸውን የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የተቀላቀሉ የምዕራብ ጎጃም ዞን ወጣቶች ተናገሩ፡፡
በሀገር ፍቅር ስሜት መከላከያን ለመቀላቀል የወሰኑ የዞኑ ወጣቶች በፍኖተ ሰላም ከተማ ሽኝት ተደርጎላቸዋል፡፡
በዚሁ ወቅት ወጣቶቹ አሸባሪው ህወሓትና ተባባሪዎች በኢትዮጵያ ላይ የጋረጡትን አደጋ በመፋለም የኢትዮጵያን ክብርና ሰላም በማስጠበቅ የአባቶቻቸውን ታሪክ እንደሚያድሱ ተናግረዋል፡፡
የመከላከያ ሙያ ሀገር በማስከበር ከሚያስገኘው የህሊና እርካታ ባለፈ ተምረው ራሳቸውን ለመለወጥ የሚያስችላቸው ክብር ያለው ሙያ በመሆኑ ዘርፉን የመጀመሪያ ምርጫቸው ስለማድረጋቸው ወጣቶቹ ገልፀዋል፡፡
ወጣቶቹ ጀግኖች አባቶች መስዋዕትነት ከፍለው ያቆዩዋትን ኢትዮጵያ ከጠላት በመጠበቅ ክብርና ሉዓላዊነቷን የማስቀጠል ታሪካዊ አደራቸውን ሊወጡ እንደሚገባ በመርሃ ግብሩ የተገኙት የአባት አርበኞች አሳስበዋል፡፡
የምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ስሜነህ አያሌው በበኩላቸው÷ ሀገር የምትመራው በትውልድ ቅብብሎሽ በመሆኑ ወጣቶች የአባቶችን የአሸናፊነት ወኔ ሰንቀው መከላከያን በመቀላቀል የሀገራቸውን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው ማሳሰባቸውን ከዞኑ መንግስት ከሙዩኒኬሽን የተገነው መረጃ አመላክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.