Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው የትህነግ ቡድን በወረራቸው አካባቢዎች ከ4 ሚሊየን በላይ ዜጎች ለከፋ አደጋ ተጋልጠዋል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል የተመራ ቡድን በትህነግ ወረራ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች አፋጣኝ የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የሚመክር ውይይት በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።
ውይይቱ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የችግሩን መጠን እና ስፋት ተገንዝቦ የተቀናጀ የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያደርስ ያለመ ነው ተብሏል።
በውይይቱ የሰላም ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል፣ የውኃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሽ በቀለ፣ የብሄራዊ የአደጋ ስጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት አስተባባሪ ዶክተር ካትሪን ሱዚ ጨምሮ የክልልና የፌዴራል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች እና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ድርጅቶች ተወካዮች ተገኝተዋል።
በአማራ ክልል ብቻ 750 ኪሎ ሜትር በሚሸፍን አካባቢ አምስት ዞኖች በሽብርተኛው ትህነግ ወረራ እንደተካሄደ የገለጹት የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ፈንታ ማንደፍሮ፥ በወረራው 4 ሚሊየን ሕዝብ ለከፋ የሰብዓዊ ቀውስ ተዳርጓል፤ 1 ነጥብ 6 ሚሊየን ሕዝብ ከመኖሪያ ቀየው ተፈናቅሏል ብለዋል።
ዶክተር ፈንታ እንዳሉት በሽብርተኛው ትህነግ ወረራ 4 ሚሊየን ሕዝብ ለከፋ የሰብዓዊ ቀውስ ተዳርጓል፤ 1 ነጥብ 6 ሚሊየን ሕዝብ ከመኖሪያ ቀየው ተፈናቅሏል፡፡
በሽብርተኛው ትህነግ ወረራ ምክንያት የሰብዓዊ ድጋፎችን በሚመለከት ከበርካታ ረጂ ድርጅቶች ጋር ተደጋጋሚ ምክክሮችን አድርገናል ያሉት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር ተግባራዊ ምላሹ ግን ከችግሩ ጋር የሚመጣጠን አይደለም ብለዋል።
አሁንም ችግሩን በቅርበት የሚያውቁ ሁሉ በትብብር እንዲሰሩ ጥሪ ማቅረባቸውን አሚኮ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.