Fana: At a Speed of Life!

የስልጠና ቆይታቸውን አጠናቀው ወደ ግዳጅ ቀጠና የተመደቡ አባላትን አቀባበል ተደረገላቸው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የስልጠና ቆይታቸውን አጠናቀው ወደ ግዳጅ ቀጠና የተመደቡ አባላትን የመተከል ኮማንድ ፖስት የተቀናጀ ግብረ ሃይል ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ አና የክልሉ ከፍተኛ የመግስት የስራ ሃላፊዎች  አቀባበል አደረጉላቸዉ።

ሌተናል ጄኔራል  አስራት ዴኔሮ ፣  ከቤተሰብ ፍቅር ከሞቀው ጎጆአችሁ ወጥታችሁ አሸባራውን ቡድን ለመደምሰስ አስፈላጊውን ወታደራዊ ስልጠና በማጠናቀቅ  የኢትዮጵያን ሕልውና እና የአባይን ግድብ ለመጠበቅ በመሰማራታችሁ ኩራት ተሰምቶኛል ብለዋል ፡፡

መሰረታዊ ወታደር አቡሽ ዳኜ እና መሰረታዊ ወታደር  አብርሃም ታምራት በሰጡት አስተያየት የተደረገላቸው አቀባበል ደስታ ፈጥሮላቸዋል፡፡

በሃገራቸው የሚቃጣ ጥቃትን ለመቀልበስ አስፈላጊውን እስከ ህይወት መሰዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን ማረጋገጣቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.