Fana: At a Speed of Life!

በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ውጤታማ የስራ አፈፃጸም ለነበራቸው የሠራዊት አባላት የማዕረግ ዕድገት ተሰጠ

አዲስ አበባ ፣መስከረም 7፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ውጤታማ የስራ አፈፃጸም ለነበራቸውና የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ የሠራዊት አባላት የማዕረግ ዕድገት ተሰጠ፡፡

በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ የፋናንስ ስራ አመራር ዳይሬክተር እና የዋና መምሪያው ተወካይ ብርጋዴር ጄኔራል ደረጀ መገርሳ ÷ መንግስት በሠራዊቱ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የሰራዊቱን መብት ለማክበር ትኩረት በመስጠት በተለየ ሁኔታ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ የሰው ሃብት ልማት መምሪያ ሃላፊ ኮሎኔል ስማቸው አናጋው ÷ ለማእረግ እድገት የበቁት አባላት በህግ ማስከበር ዘመቻ ተሳትፈው የላቀ ውጤት ያመጡ አባላት በልዩ ሁኔታ እና የመቆያ ጊዜያቸውን የሸፈኑ አባላት ናቸው ብለዋል፡፡

በዚህም ከምክትል አስር አለቃ እሰከ ሙሉ ኮሎኔል በጠቅላላ 150 የዋና መምሪያው አባላት በሚመለከተው አካል ፀድቆ ለማእረግ እድገት እንዲበቁ ተደርጓል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ፌስ ቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.