Fana: At a Speed of Life!

የመከላከያ ሚንስትሩ በ“ነጩ ፖስታ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት” ንቅናቄ ፊርማቸውን አኖሩ

አዲስ አበባ ፣መስከረም 7፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የመከላከያ ሚንስትሩ ዶክተር ቀነዓ ያደታ በ“ነጩ ፖስታ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት” ንቅናቄ ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡

ሚኒስትሩ የንቅናቄው ዋና አላማ ፣ የኢትዮጵያውያን እውነታ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማሳወቅ፣ የአሸባሪውን ህወሓት አገር የማፍረስ ወረራ ማጋለጥ መሆኑን ገልፀዋል።

መንግስት የህዝቦችን ደህንነት እና የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ የሚወስደውን ህጋዊ ርምጃ አሜሪካ እና ምዕራባውያን በማወቅ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ እና ባለማወቅ በተሳሳተ መረጃ በኢትዮጵያ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደሩ መሆናቸውን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡

ዶክተር ቀንዓ እንዳሉትም አሸባሪው የህወሓት ቡድን ንጹሃን ዜጎችን በመጨፍጨፍ፣ ዜጎች ለዘመናት ያፈሩትን ሃብትና ንብረት በማውደም፣ ከህጻናት እስከ አዛውንት ያሉ ሴቶች መድፈርን ጨምሮ ሌሎች ግፎችን መፈጸሙን ተናግረዋል።

የጥፋት ሀይል በማይካድራ፣ አጋምሳና ጭና እንዲሁም ጋሊኮማ ላይ ንፁሃን ዜጎችን በመጨፍጨፍ አሸባሪነቱን በተግባር አረጋግጧል ያሉ ሲሆን ÷“የነጩ ፖስታ ለነጩ ቤተ-መንግስት” የፖስታ መልዕክት ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጠቀሜታ እንደሚኖረው መግለፃቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ፌስ ቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.