Fana: At a Speed of Life!

ደም መለገስ ለእኛ ትንሹ ግዴታ ነው – የጎንደር ፋና ኤፍ ኤም ሰራተኞች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ደማችንን ለሠራዊታችን” በሚል መሪ ቃል ደም የጎንደር ፋና ኤፍ ኤም 98.1 ሬዲዮ ጣቢያ ሰራተኞችና ተባባሪ አዘጋጆች በዛሬው ዕለት ለሀገር ህልውና እየተዋደቀ ላለው የወገን ጦር ደም ለግሰዋል።

ለኢትዮጵያ ህልውና በሙያችን ከምናበረክተው አስተዋጽኦ በተጨማሪ ደማችንን ግንባር ላይ ዘምተው ለሚገኙ ጀግኖች ደም በመለገሳችን ይህ ለእኛ ትንሹ ግዴታ ነው ሲሉ ሰራተኞች ተናግረዋል።

የጣቢያው ስራ አስኪያጅ አቶ ነብዩ ዮሐንስ ፥ለኢትዮጵያ ክብር፣ ነፃነት፣ ሰላምና የግዛት አንድነት መጠበቅ ያለንን ሁሉ ለመስጠት ዝግጁ ነን ብለዋል።

ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሚችለው ሁሉ የኢትዮጵያን የውስጥና የውጭ ጠላቶች ለመመከትና ለማሸነፍ መሰለፍ አለበት ነው ያሉት።

በገንዘብና በቁሳቁስ ከሚደረገው የደጀንነት ሚና በተጨማሪ ህይወቱን እየሰጠ ላለው የወገን ጦር የደም ልገሳ በማድረግም ሀላፊነትን መወጣት ያስፈልጋል ብለዋል።

የደም ልገሳ ያደረጉት የተቋሙ ጋዜጠኞች፣ የአስተዳዳር ሰራተኞችና ተባባሪ አዘጋጆች ደም መለገስ ለሰጪው የአእምሮ ሰላም ለተለጋሾች ደግሞ ህይወትን የሚሰጥ በመሆኑ ድጋፋችን ይቀጥላል ብለዋል።

ከደም ልገሳው በተጨማሪ ዜጎች ለህልውናቸውና ለሀገራቸው ክብር ሲሉ የመከላከያ ሰራዊትን በመቀላቀል ሀገራዊ ግዴታን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

በዚህ ወቅት ተገኝተው ምስጋና ያቀረቡት የጎንደር ደም ባንክ ሀላፊው አቶ ደመቀ ጥላሁን በበኩላቸው÷ ዜጎች እያበረከቱት ያለው አስተዋፅኦ የሚበረታታ ነው ብለዋል።

ባለፉት ሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ 3 ሺህ 600 ያህል ዩኒት ደም በመሰብሰብ ዘማቾች ለሚታከሙባቸው የህክምና ተቋማት እያሰራጩ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በሙሉጌታ ደሴ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.