Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ምሁራን በወቅታዊ ሀገራዊ ና ክልላዊ ሁኔታ ላይ ውይይት እያካሄዱ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ለፍትሕ እና ርትዕ መታገል የምሁራን ኀላፊነት ነዉ” በሚል መሪ ሐሳብ የአማራ ምሁራን በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ሁኔታ ላይ ውይይት እያካሄዱ መሆኑ ተገለጸ።
የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ አብርሃም አለኸኝ በመድረኩ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፥ ሽብርተኛው ትህነግ ወረራ በፈጸመባቸው የአማራ እና የአፋር ክልሎች የከፋ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጥፋቶችን ማድረሱን አንስተዋል።
አሸባሪው ቡድን የፈጸመውን ወረራ ለመመከት የህልውና ዘመቻ በመታወጁና ህዝቡ በአንድነት በመነሳቱ ወራሪው ዳግም በማይነሳበት ሁኔታ እየተመታ ነው ብለዋል፡፡
አሸባሪው የትህነግ ወራሪ ቡድን ጦርነት ቢከፍትብንም ጦርነቱ ከፍ ባለ ደረጃ የህዝብ አንድነት ያመጣ መሆኑን አቶ አብረሃም ገልጸዋል፡፡ በዚህ ረገድ የክልሉ ምሁራን ያላሰለሰ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አሳስበዋል።
አቶ አብርሃም እንዳሉት አሸባሪውን ትህነግ ለመደምሰስ የምሁራን ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በቀጣይ በርካታ ሥራ ይጠበቅባቸዋል፤ አሽባሪው ትህነግ አማራን ብሎም ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሙከራ ቢያደርግም አይሳካለትም ብለዋል፡፡
ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች መልሶ ለመገንባትና በወራሪው የተያዙ ቦታዎችን ለማስለቀቅ እንዲሁም በቀጣዩ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ እንቅስቃሴ ላይ ምሁራን ድርሻቸው የጎላ መሆኑን አብራርተዋል።
ሽብርተኛው የትህነግ ወራሪ ቡድንን መደምሰስ ብቻ ሳይሆን ትግራይ ላይ ተቀምጦ የባንዳነት ተግባሩን እንዳይወጣ ሴራውን ለመበጣጠስ የምሁራን ሚና ከፍተኛ መሆኑንም ሃላላፊው ጠቁመዋል።
በውይይቱ የተፎካካሪ ፓርቲ አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው የዩኒቨርስቲ ምሁራን እየተሳተፉ መሆኑን አሚኮ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.