Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባን በመወከል በዓለም አቀፍ የስእል ውድድር አሸናፊ የሆኑ ታዳጊዎች ሽልማታቸውን ተቀበሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባን በመወከል በደቡብ ኮሪያዋ ቹንቹን ከተማ በተካሄደው ዓለማቀፍ የስእል ውድድር አሸናፊ የሆኑ ታዳጊዎች ሽልማታቸውን መቀበላቸው ተገለፀ፡፡

በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ ኤምባሲ ምክትል ተጠሪ ኪም ሂዮን ዱ ÷በቹንቹን ከተማ ከንቲባ ስም ሽልማቱን ለአሸናፊ ታዳጊዎች አስረክበዋል፡፡

ኪም ሂዮን ዱ በኢትዮጵያ እና በደቡብ ኮሪያ መካከል ያለው ታሪካዊ ወዳጅነት ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ መሆኑን አንስተው÷ በአዲስ አበባና ቹንቹን ከተሞች መካከል ያለውን ሁለተናዊ ግንኙነት በተለያዩ ዘርፎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማስታወቃቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.