Fana: At a Speed of Life!

የጤና ሚኒስቴር ከፖሊሽ ሴንተር ፎር ኢንተርናሽናል ኤይድ ጋር በጋራ ለመስራት ተስማማ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር የድንገተኛ አደጋ እና የፅኑ ህክምና አገልግሎት ለማሻሻል ከፖሊሽ ሴንተር ፎር ኢንተርናሽናል ኤይድ ጋር ለሶስት አመት የሚቆይ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡

ስምምነቱ ለአንቡላንስና ድንገተኛ አደጋ ህክምና የሚውሉ ግብአቶችን ማቅረብ፣ ለድንገተኛ ህክምናና ፓራሜዲክ ባለሞያዎች ስልጠና፣ የቅድመ ጤና ተቋም አገልግሎትን ለማሳለጥ የጥሪ እና ስምሪት ማዕከል ማጠናከር፣ ለትራፊክ እና በጅምላ ለሚደርሱ አደጋዎች ምላሽ አሰጣጥን የሚያሻሽሉ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎችን ያካትታል ተብሏል፡፡

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ÷ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ በፖላንድ መንግስት የሚደገፍ መሆኑን ገልፀው ÷ጠንካራ የጤና ስርዓት ለመገንባትም አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡

ለድጋፉም ለፖላንድ መንግሥት እንዲሁም ለፖላንድ ዓለም አቀፍ ዕርዳታ ማእከል ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.