Fana: At a Speed of Life!

አቶ ወርቁ አይተነው በወሎ ግንባር ለተፈናቀሉ ዜጎች 100 ሚሊየን ብር መደቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ሳቢያ በወሎ ግንባር ከቤታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ለድጋፍ የሚሆን 100 ሚሊየን ብር መመደባቸውን አስታወቁ።
ባለሀብቱ ትናንት እና ዛሬ ለተፈናቃዮች ለአልባሳትና ምግብ ነክ ግዥ 25 ሚሊየን ብር ወጪ አድርገዋል።
አቶ ወርቁ ለፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት÷ ደብሊው ኤ በተሰኘው ድርጅታቸው 100 ሚሊየን ብር መመደባቸውን ጠቁመው በንግዱ ማህበረሰብ በተደረገ መዋጮ ደግሞ 40 ሚሊየን ብር ወጪ አድርገዋል።
በተመሳሳይም አሸባሪው ህወሓት በአፋር ግንባር ላደረሰው ጉዳት ለተፈናቀሉ ዜጎች 50 ሚሊየን ብር በግላቸው መለገሳቸው ይታወሳል።
እንደ አቶ ወርቁ ገለፃ÷ ልገሳው ጊዜያዊ ሲሆን በቀጣይ ዜጎች በቀያቸው እስኪቋቋሙ ድረስ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
አሸባሪውን ህወሓት እስከመጨረሻው ለመደምሰስ ወጣቶች ከሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ ከአማራ ክልል እና ሌሎች ክልሎች ልዩ ኃይሎችና ሚሊሻዎች ጋር ተሰልፈው እንዲፋለሙም ጥሪ አቅርበዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.