Fana: At a Speed of Life!

አረመኔው የህወሓት ቡድን ንፁሃንን በጅምላ በመረሸን ዓለም አቀፍ ወንጀል ፈፅሟል- ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)  አረመኔውና ከሃዲው  የህውሓት ቡድን ንፁሃንን በጅምላ በመረሸን ዓለም አቀፍ ወንጀል ፈፅሟል ሲሉ በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ ገለጹ።

የፌደራል መንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የመገናኛ ብዙሃንና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮች በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ ጭና ቀበሌ በአሸባሪው በድን በግፍ የተጨፈጨፉ ወገኖችን የቀብር ቦታ መጎብኘታቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።

የማዕከሉ አስተባባሪ  ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ  በጉብኝቱ ላይ እንዳሉት አሸባሪው የህወሓት ቡድን ለ27 ዓመት የኢትዮጵያን ህዝብ እርስ በእርስ ሲያባላና እንዲጠራጠር ሲያደርግ የኖረ የክፉዎች ስብስብ ነው።

ቡድኑ ዛሬ ላይ ኢትዮጵያውያንን ካላጠፋሁ በማለት ንፁሃንን በጅምላ በመረሸን ዓለም አቀፍ ወንጀል እየፈፀመ መሆኑን አብራርተዋል።

“የጭና ህዝብ ከፍተኛ መስዋትነት በመክፈል ኢትዮጵያን ለማፈራረስ አስቦ የመጣውን ወራሪ ሃይል ቅስም በመስበር ለመላው ኢትዮጰያዊያን ባለውለታ ሆኗል”ብለዋል።

“አሸባሪው ቡድን ዳግም በኢትዮጵያ ምድር መሰል ዘግናኝ ግፎችንና ጭፍጨፋዎችን እንዳይፈፅም  በኢትዮጵያዊያን የተባበረ ክንድ ይደመሰሳል” ሲሉም ተናግረዋል።

“መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በጭና ህዝብ ላይ በደረሰው ጭፍጨፋ ልቡ ተሰብሯል” ያሉት ዶክተር ቢቂላ የጠፋው ንብረትም ሆነ የፈረሰው መኖሪያ ቤት በኢትዮጵያውያን ለጋስ እጆች ዳግም ወደ ነበረበት ይመለሳል” ብለዋል።

አሸባሪው ቡድን ንፁሃንን በግፍ በመጨፍጨፍ እየፈፀመ ባለው ድርጊት በዓለም አቀፍ ወንጀል የሚጠየቅበት ጊዜም ሩቅ እንደማይሆን እምነታቸውን ገልፀዋል።

የስራ ሀላፊዎችና የአመራር ቡድኑ በግፍ የተጨፈጨፉ ወገኖችን የቀብር ቦታ፣ በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች፣ በማይፀብሪ ግንባር እየተፋለመ የሚገኘውን የፀጥታ ሃይል የመጎብኘትና የማበረታታት ስነ ስርዓት አካሄዷል።

የስራ ሀላፊዎችና የአመራር ቡድኑ በሌሎች አካባቢዎችም ጉብኝቱን እንደቀጠለ ለማወቅ ተችሏል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.