Fana: At a Speed of Life!

የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለመቀላቀል ዝግጁ የሆኑ ወጣቶች ሽኝት ተደረገላቸዉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባል የመሆን ጥሪን የተቀበሉ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምልምል የመከላከያ ሰራዊት ወጣቶች ሽኝት ተደረገላቸዉ።

ሽኝት የተደረገላቸዉ ምልምል የመከላከያ ሰራዊት አባላት በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ ወጣቶች ናቸዉ።

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ብልጽግና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ አምሳል አማረ ÷ዞኑ ከአሁን በፊት ሀገርን ከወራሪ ለመከላከል በሚደረገዉ ጥረት በሁለት ዙር ምልምል የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ወደ ስልጠና ማዕከል መላኩን አስረድተዋል።

የጽሕፈት ቤት ኀላፊዉ በሶስተኛዉ ዙር መርሃግብርም ሀገር ወዳድ ወጣቶች ተመዝግበዉ መስፈርቱን ያሟሉ ወደ ማሰልጠኛ ማዕከል እንደተሸኙ ተናግረዋል።

ሽኝት የተደረገላቸዉ ምልምል የሰራዊት አባላት በማሰልጠኛ ማዕከልም ይሁን በግዳጅ በተሰማሩባቸዉ ቦታዎች ሙያዊ ግዴታቸዉን እንዲወጡ አቶ አምሳል መልዕክት አስተላልፈዋል።

ምልምል ወጣቶቹም ስልጠናቸዉን አጠናቀዉ የሀገራቸዉን ዳር ድንበር ለማስከበርና ወራሪዉን የትህነግ ቡድን ለመደምሰስ ዝግጁ እንደሆኑ መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.