Fana: At a Speed of Life!

በግብረ-ኃይሉ የቁጥጥር ሥራ የዋጋ ቅናሽ ተስተውሏል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለዘመን መለወጫ በዓል ለግብይት የቀረቡ ምርቶች ላይ የዋጋ ቅናሽ እንደተስተዋለ ተገለጸ፡፡

ይህ የተገለጸው የዋጋ ንረትና የኢኮኖሚ አሻጥርን ለመከላከለ በፌዴራል፣ በክልሎች እና በከተማ አስተዳደሮች ደረጃ የተዋቀረው ግብረ ሃይል የሰራቸውን መጠነ ሰፊ ስራዎች ለንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት ነው፡፡

ግብረ ሃይሉ ባቀረበው ሪፖርት መሰረት አንዳንድ ምርቶች የዋጋ ጭማሪ ሳይደረግባቸው ባሉበት መቆየታቸው ነው የታወቀው፡፡

ከግብርና ምርቶች የነጭ ጤፍ፣ የቀይ ጤፍ፣ የበቆሎ፣ የሩዝና የስንዴ ዋጋ መጠነኛ ቅናሽ ያሳየ ሲሆን ከኢንዱስትሪ ውጤቶች ደግሞ በምግብ ዘይት ዋጋ ላይ ቅናሽ መታየቱ ተመላክቷል፡፡

በሌላ በኩል የቀይ ሽንኩርት ዋጋ ከሣምንታት በፊት ሲሸጥ ከነበረበት ዋጋ በእጅጉ የጨመረ በመሆኑ ግብረ-ኃይሉ በቀጣይ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያደረገ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር መላኩ አለበል÷ ግብረ-ኃይሉ ሕዝብና መንግስት የጣለበትን ሃላፊነት በመልካም ዲሲፒሊን እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ መሰራት የሚገባቸው በርካታ ተግባራት መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡

እነዚህን ቀሪ የቤት ስራዎች ለመስራት ከግብረ-ኃይሉ በተጨማሪ የሁሉም የሕብረሰብ ክፍል ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑም በመድረኩ ተገልጾ በሀገሪቱ ላይ የተረጋጋ የኢኮኖሚ ፍሰት እንዲኖር ከምንጊዜውም በላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራም መናገራቸውን ከንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.