Fana: At a Speed of Life!

ጀርመን ከ271 ሺህ ዶዝ በላይ የኮቪድ-19 ክትባት ለኢትዮጵያ ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጀርመን መንግስት 271 ሺህ 200 ዶዝ አስትራዜኒካ የኮቪድ-19 ክትባትና 900 ሺህ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛለኢትዮጵያ ድጋፍ አደረገ፡፡

በኢትዮጵያ የጀርመን ምክትል አምባሳደር ሄይኮ ኒሽኬ ክትባቱን ለጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስረክበዋል።

ዶክተር ሊያ በአገር አቀፍ ደረጃ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭትን ለመግታት ክትባት በስፋት እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ከሚያደርጉት ድጋፍ በተጨማሪ በመንግስት ወጪ ክትባቱ እየተገዛ መሆኑን ገልፀው በዚህም በአገር አቀፍ ደረጃ 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሰዎች መከተባቸውን ተናግረዋል፡፡

የጀርመን መንግስት ያበረከተው አስትራዜኒካ ክትባቱን በስፋት ለመስጠት የሚያስችል እንደሆነ የገለፁት ዶክተር ሊያ የመጀመሪያውን ክትባት ለወሰዱ ሰዎች ሁለተኛ ዙር መስጠት እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡

ክትባቶቹ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እየተሰጡ መሆናቸውን የገለጹት ዶክተር ሊያ ዜጎች ያለምንም ስጋት እንዲከተቡ አሳስበዋል፡፡

ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች 3 ሚሊዮን ዶዝ የሚጠጋ አስትራዜኒካ፣ ጆንሰን እና ጆንሰን እንዲሁም ሳይኖፋርም የኮቪድ ክትባቶች በድጋፍ መገኘታቸውን ገልፀዋል፡፡

ድጋፉ ከአፍርካ ኅብረት፣ ከዓለም የጤና ድርጅት፣ ከዩኒሴፍና ኮቫክስ መገኘቱን የገለፁት ሚኒስትሯ ተቋማቱ ድጋፋቸውን እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ የጀርመን ምክትል አምባሳደር ሃይኮ ኒች የክትባት ድጋፉ አገራቸው የቫይረሱን ስርጭት በጋራ ለመከላከል የምታደርገው ጥረት አካል መሆኑን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.