Fana: At a Speed of Life!

የዓለም አቀፍ የፅዳት ቀን በመዲናዋ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ንፁህና ፅዱ ትምህርት ቤት ለትውልድ “በሚል መሪ ቃል የዓለም አቀፍ የፅዳት ቀን በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ተካሄደ፡፡
የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የጽዳት ዘመቻ መርሐግብር በትምህርት ቤቶች መካሄዱ÷ ተማሪዎች በኮቪድ-19 ወረርሽኝ እንዳይጠቁ ከማድረግ ባለፈ ንጹሕ እና ጽዱ ትምህርት ቤቶችን ለመፍጠር ያስችላል ተብሏል፡፡
የትምህርት ሚንስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ፣ የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሀመድ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት፣ ተማሪዎች፣ መምህራን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በእቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ትምህርት ቤትን ማጽዳታቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.