Fana: At a Speed of Life!

በምክትል አፈ ጉባኤ ሽታዬ ምናለ የሚመራ ልኡክ ኮምቦልቻ ገባ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምክትል አፈ ጉባኤ ሽታዬ ምናለ የተመራ የሴት ሚኒስትሮችን ያካተተ ልዑክ ኮምቦልቻ ገብቷል፡፡
ምክትል አፈ ጉባኤ ሽታዬ ምናለ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ካሳው ፣ የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስን ጨምሮ ሌሎችም የፌደራል ከፍተኛ ባለስልጣናትና ሚኒስትሮች ናቸው ኮምቦልቻ የገቡት።
የልኡክ ቡድኑ ኮምቦልቻ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል ተደርጎለታል።
ምክትል አፈጉባኤዋና ሚኒስተሮቹ በደሴ የሚገኙ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዬችን እንደሚጎበኙ እና ውይይት እንደሚደርጉ ይጠበቃል፡፡
በሀብታሙ ተ/ስላሴ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.