Fana: At a Speed of Life!

ተመራቂዎች በሚሰማሩበት ሙያ በታማኝነትና በቅንነት ለሀገራቸው ሊሠሩ እንደሚገባ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ተመራቂዎች በዩኒቨርሲቲዉ ያገኙትን እዉቀት ወደ ፈጠራና የስራ እድሎች በመቀየር ለሌሎችም ጭምር መለወጥ ማመቻቸት እንደሚገባ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፋ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ገለፁ፡፡
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህት መርሃ ግብሮች ሲያስተምራቸዉ የነበረዉን 6,793 ተማሪዎችን ዛሬ አስመርቋል፡፡
የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት ዶክተር አያኖ በራሶ በኮሮና ችግር ምክንያት ተማሪዎች ሊመረቁ ከሚገባቸዉ ጊዜ 2 ወራት ዘግይቷል ብለዋል፡፡
የመንግስት የልማት የትኩረት መስኮችን በመለየት የምርምር ስራዎችን በመስራት ለዉጤት መብቃት መቻሉንም ነው የተናገሩት፡፡
ዩኒቨርሲቲዉ ኮቪድ-19 በተንሰራፋበት ወቅት በዩኒቨርሲቲዉ ሆስፒታል ማቆያ በማዘጋጀት ከሲዳማ ክልል፣ ደቡብ ክልል አጎራባች ዞኖችና ደቡብ ኦሮሚያ ዞኖች የሚመጡ ታማሚዎችን ማቆያ አዘጋጅቶ ሲያክም መቆየቱንም ገልፀዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲዉ በ2014 በሁለተኛ ዲግሪ 20፣ በ3ኛ ዲግሪ 20 የትምህርት መስኮችን በመክፈት ለማስተማር ምዘገባ ላይ መሆኑንም ዶክተር አያኖ ተናግረዋል።
የ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ለተመራቂዎች በሚሰማሩበት መስክ ግልፅ ራዕይ፣ ጤናማ ስብዕናና ጠንካራ የስራ ትጋት ሊኖራቸዉ እንደሚገባ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።
ዩኒቨርሲቲዉ ዛሬ ሲያስመርርቅ ለ22ኛ ጊዜ መሆኑ ነው ተብሏል፡፡
በጌታቸዉ ሙለታ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.