Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከአሜሪካ የኮንግረስ አባል ካረን ባስ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአሜሪካ የኮንግረስ አባል እና የካሊፎርኒያ ግዛት ተወካይ ካረን ባስ ጋር በሁለትዮሽ እና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም አቶ ደመቀ መኮንን ለአሜሪካ ህዝብ ተወካዮች አባል ካረን ባስ እና የልዑካን ቡድናቸው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልክት አስተላልፈዋል።
አሜሪካ ኢትዮጵያ ኮቪድ 19ኝን ለመቆጣጠር እያደረገችው ያለውን ጥረት ለማገዝ የክትባትና መሰል ድጋፎችን ማድረጓ የሚያስመሰግናት መሆኗንም ተናረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር በኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ዘርፎች ግንኙነቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል እና የቀጠናውን ሰላም ለማረጋጋት በተለይም ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ከአገሪቱ ጋር በጋራ እንደምትሰራም አስረድተዋል፡፡
የኮንግረስ አባሏ በአሜሪካ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያ እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር የኢትዮጵያን ሰላም ማስቀጠል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ለመወያየት ያሳዩት ፍላጎትና ተነሳሽነት የሚያስመሰግናቸው መሆኑን አቶ ደመቀ ገልፀውላቸዋል፡፡
በወንደሰን አረጋኸኝ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.