Fana: At a Speed of Life!

ለአንድ ወር ያልተቋረጠው አጥሚት የማዘጋጀት በጎነት

አዲ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አቶ አብደላ መሀመድ ላለፉት 30 ቀናት ያለማቋረጥ አጥሚት በማዘጋጀት ለወገን አለኝታነታቸውን በተግባር አረጋግጠዋል፡፡
አቶ አብደላ አንሷር መሀመድ የገንዳውሃ ከተማ ነዋሪ ናቸው።
እኒህ ግለሰብ በመተማ ሆስፒታል በመተማ ሽንፋ ግንባር በነበረው ዉጊያ የቆሰሉ የፀጥታ አካላትን ቀን በቀን አጥሚት በማዘጋጀት ይጠይቃሉ።
ግለሰቡ ከነሃሴ 27 ጀምሮ አራት ባልዲ አጥሚትን ራሳቸው አዘጋጅተው በሆስፒታሉ የህክምና ክትትል ለሚደረግላቸው የወገን ሰራዊት ዕለት ተዕለት ያቀርባሉ።
አሸባሪው የህውሓት ቡድን በከፈተው ጦርነት የተጎዶ ወገኖችን ለመደገፍ ሀብታም መሆን አይጠይቅም የሚሉት አቶ አብደላ÷ እኔም ብርታት ይሰጣቸዋል ብዬ ያሰብኩትን አጥሚት ለማዘጋጀት ፈቅጃለሁ ብለዋል።
በቀናት ሂደት ውስጥ ያልተቋረጠው የግለሰቡ የአጥሚት መጠየቂያ ተግባር በቀጣይም የሽብር ቡድኑ እስኪ ደመሰስ ድረስ እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
በመተማ ሆስፒታል የህክምና ክትትል የሚደረግላቸው የሰራዊት አባላት አቶ አብደላ የሚያዘጋጁት አጥሚት ብርታት እየሰጣቸው መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
ካላቸው ገቢ ይህን ማድረጋቸው በአጭር ጊዜ አገግመን ጠላትን ድል እንድናደርግ የውስጥ ብርታት ሆኖናልም ነው ያሉት፡፡
የሚያውቋቸው የቅርብ ጓደኞቻቸው የግለሰቡ ተግባር ለሌሎች ጥሩ ምሳሌ እንደሚሆንም ጠቁመዋል፡፡
ምናለ አየነው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.