Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ”የነጩ  ፓስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተመንግሥት”  ደብዳቤ የመጻፍ መርሐግብር አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና የካቢኔ አባላት “የነጩ  ፓስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተመንግሥት”  ደብዳቤ የመጻፍ መርሐግብር አስጀምረዋል፡፡

“የነጩ ፓስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተመንግሥት”  በሚል የውጪ ሀገራት በተለይ የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት እና የኢትዮጵያን እውነት ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ለማስረዳት ያለመ  ሀገር አቀፍ ደብዳቤ የመጻፍ የፊርማ ማሰባሰብ ንቅናቄ መርሐግብር በቅርቡ በይፋ መጀመሩ የሚታወስ ነው።

በዛሬው ዕለትም ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና የካቢኔ አባላት “የነጩ  ፓስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተመንግሥት”  ፊርማ  የማሳረፍ መርሐግብር አካሂደዋል፡፡

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በፊርማ መርሐ-ግብሩ ላይ ፥ የኢትዮጵያ ወጣቶች የሀገሪቱን እውነት ዓለም እንዲረዳው ለማድረግ የጀመሩት  “የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተመንግሥት” የተሰኘው ሀገር ዓቀፍ ንቅናቄ ከምንም በላይ ኢትዮጵያ  የወጣቶቿን ሁለንተናዊ ድጋፍ በሁሉም መስክ በምትሻበት ጊዜ በመሆኑ ሊበረታታ እና ሊመሰገን የሚገባው ተግባር ነው ብለዋል፡፡

የህውሓት አሸባሪ ቡድን በኢትዮጵያ ሕዝብና ወጣቶች ላይ እጅግ አሰቃቂ የሰብአዊ መብት ጥሰት አድርሷል ፣የኢትዮጵያ ሀብት ዘርፏል ፣ይህ ሁሉ አልበቃ ብሎት ጥቅምት 24 በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ፈጽሟ ፣በመላ ሀገሪቱም የሽብር ወንጀሎችን  እየፈጸመ ይገኛል ብለዋል ምክትል ከንቲባዋ ።

ቡድኑ በአሁኑ ወቅትም በአፋር እና አማራ ክልሎች ላይ ወረራ በመፈጸም  ሰብዓዊ ቀውስ እያደረሰ ይገኛል ያሉት ምክትል ከንቲባዋ ፥ ይህን የቡድኑን እኩይ የአሸባሪነት ተግባር ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ልናሳውቅ ይገባል ማለታቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሰክሬተሪያት ቢሮ  ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.