Fana: At a Speed of Life!

ዘመቻውን አሸንፈን እኩልነትና ፍትሐዊነት የሰፈነባት የጋራ ኢትዮጵያን እንገነባለን-የአብን የውጭ ግንኙነት ኃላፊ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕልውና ዘመቻውን አሸንፈን አንድነት፣ እኩልነትና ፍትሐዊነት የሰፈነባት የጋራ ኢትዮጵያን እንገነባለን ሲሉ የአብን የውጭ ግንኙነት ኃላፊ ዶክተር ቴዎድሮስ ኃይለማርያም ተናገሩ።
የተደቀነውን የህልውና ስጋት መቀልበስ፤ ወንጀለኞችን ለፍርድ ማቅረብ እንዲሁም የአሸባሪውን ህወሃት አስተሳሰብ በማክሰም አንድነት እኩልነትና ፍትሐዊነት የሰፈነባት የጋራ ኢትዮጵያን መገንባት ደግሞ የህልውና ዘመቻው ዋነኛ ግቦች መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ዶክተር ቴዎድሮስ ይህን ያሉት በደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ እየተካሄደ ባለው የምሥራቅ አማራ ዩኒቨርሲቲዎች የምሁራን ምክክር መድረክ ላይ የመወያያ ፅሁፍ ባቀረቡበት ወቅት ነው።
አሸባሪው ህወሓት የአማራ ህዝብን ስነ-ልቦና ለመጉዳት ለዓመታት በርካታ ግፎችን ሲፈጽም መቆየቱን አንስተዋል።
አሸባሪ ቡድኑ አሁን ላይ የእምነት አባቶችን ጨምሮ ሰላማዊ ዜጎችን በመግደል፣ ሴቶችን በመድፈር፣ የእምነት ተቋማትን ጭምር የህዝብ ሃብትን በመዝረፍና በማውደም ግፍ መፈጸሙንም ነው የተናገሩት።
አሸባሪ ቡድኑ የትግራይ ህዝብን ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወንድሞቹ ለመነጠል ሲሰራ መቆየቱን ጠቅሰው፤ ላለፉት 50 ዓመታት በአማራ ጥላቻ የታወረ ትውልድ ለመፍጠር በርካታ ሴራዎችን አከናውኗል ነው ያሉት።
“ህዝብን ለመታደግ ከአውደ ውጊያ በተጨማሪ በፕሮፓጋንዳ፣ በዲፕሎሚሲና በሚዲያ መዝመት ይገባል፤ ምሁራንም ይህን ዕድል መጠቀም አለባቸው” ብለዋል።
በተጨማሪ ለዘመቻው የሎጅስቲክስና የፋይናንስ ድጋፍ በማድረግ ደጀንነታችንን ማሳየት አለብን ሲሉም ነው የገለጹት።
አሸባሪው ህወሓት ሸኔን ከመሰሉ ፀረ-ህዝብና ኢትዮጵያን በማፍረስ ዓላማ የቆረቡ የውስጥ ኃይሎች ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ጠቅሰው፤ በሁሉም መስክ ዝግጁነታችንን በማጠናከር የእነዚህን ቡድኖች ዓላማ ማክሸፍ አለብን ብለዋል።
በውክልና ጦርነት የሚሳተፉ ታሪካዊ የውጭ ጠላቶች እንዳሉ ሁሉ ወዳጅ አገራት መኖራቸውን ተገንዝበን በዲፕሎማሲው መስክ ጠንካራ ስራ ማከናወን እንደሚገባም ዶክተር ቴዎድሮስ ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
ምሁራን ችግሩን ዓይነትና መጠን በመተንተን፣የፖለቲካ ኃይሎችን በማደራጀትና ማህበረሰብን በማንቃት፣ አሸባሪው ህወሃት ሀገር የማፍረስ ተግባርን በመመከት ብሎም በማጥፋት ረገድ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 10 people, people sitting and indoor
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.