Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና ግዛታዊ አንድነትን ለማስጠበቅ እየተካሄዱ ያሉ ተግባራትን እንደምትደግፍ የሀገሪቱ የኮንግረስ አባላት ገለፁ

አዲስ አበባ፣ መስረም 8፣ 14 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የአሜሪካ የኮንግረስ አባላትን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
ለኮንግረስ አባላቱም ኢትዮጵያ የሕግ የባላይነትን ለማስጠበቅ እያካሄደችው ባለው ተግባር ዙሪያ ገለጻ አድርገውላቸውዋል፡፡
በዚህ ወቅት የልዑካን ቡድኑ ዓባላት አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ላላት የቆየ ወዳጅነት ትልቅ ቦታ እንደምትሰጥ ተናግረዋል፡፡
አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የረጅም ጊዜ ወዳጅነት በተለያዩ የትብር መስኮች አጠናክራ ለማስቀጠል ቁርጠኛ መሆኗን የኮንግረስ አባላቱ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ እያደረገችው ላለው ጥረት አሜሪካ ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥልም የኮንግረስ አባላቱ ቃል ገብተዋል፡፡
እንዲሁም የተለያዩ የትብብር መስኮች እና የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ለማጠናከር የምትሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ኢትዮጵያ ወደ ሕግ ማስከበር በገባችባቸው ገፊ ምክንያቶችና አሸባሪው የህወሓት ቡድን በንፁሃን ዜጎች ላይ እያደረሰ ባለው ኢ ሰብዓዊ ድጊት ላይ ሰፊ ማብራሪያ መስጠታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡
በወንደሰን አረጋኸኝ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 2 people, people sitting and people standing
65,501
People Reached
3,645
Engagements
Boost Post
1.6K
144 Comments
95 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.