Fana: At a Speed of Life!

መከላከያ ሰራዊቱን በመቀላቀል እና ስልጠና በመውሰድ ሀገራችንን እጠብቃለን- የመቄት ወረዳ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፋላቂት ከተማ የመቄት ወረዳ ነዋሪዎች ከተለያዩ ቀበሌዎች የተውጣጡ በርካታ ነዋሪዎች የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊትን ለመቀላቀል እና ስልጠና ለመውሰድ በነቂስ ወጥዋል።
የህወሓት የሽብር ወረራ ከፈፀመባቸው አካባቢዎች የመቄት ወረዳ አንዱ ሲሆን፥ ቡድኑ በቆየባቸው አንድ ወር ከአስር ቀናት ውስጥ በርካታ ኢሰብአዊ ድርጊቶቹን በመፈፀሙ ነዋሪዎቹ ለከፍ ችግር ተጋልጠዋል።
በዚህም ዛሬ በፍላቂት ከተማ በሺህዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች መከላከያ ሰራዊቱን ለመቀላቀል እና ስልጠና ለመውሰድ ወጥተዋል።
ይህንንም በማድረግ ሀገራችንን እጠብቃለን ያሉት ነዋሪዎቹ፥ ከዚህ በላይ ምንም ችግር እና መከራ ሊደርስብን አይችልም ሲሉ ገልጸዋል።
የሽብር ቡድኑን የፈፀመውን አስነዋሪ ድርጊት በእጅጉ እንዳስከፋቸው ተናግረዋል።
በምንይችል አዘዘው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.