Fana: At a Speed of Life!

በቀመጫቸውን ጅቡቲ ያደረጉ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ዘመናዊ ቄራ ለመገንባት ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት የተውጣጡ መቀመጫቸውን ጅቡቲ ያደረጉ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ዘመናዊ ቄራ ለመገንባት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።
ባለሀብቶቹ በኢትዮጵያ ለሦስት ቀናት የኢንቨስትመንት ጉብኝትያደረጉ ሲሆን፥ ከከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ፣ ከሚመለከታቸው የሥራ ሃላፊዎች እንዲሁም በአገሪቱ ካሉ የግሉ ዘርፍ ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።
በዚሁ ወቅት የልዑካን ቡድኑ ኃላፊ ሙስጠፋ ጃማ፥ አዲሱ የሚገነባው ዘመናዊ ቄራ ለእርድ የሚቀርቡ እንስሳቶችን ከማደለቢያ አንስቶ እስከ እርድ የሚኖረውን ሂደት ለአውሮፓ እና ሌሎች ደረጃቸውን ለጠበቁ ገበያዎች ሙሉ መረጃ ለማቅረብ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።
በተጨማሪም መርሃግብሩ ተግባራዊ ሲደረግ የመድኃኒቶችን እና የእንስሳት ጤና አያያዝን እንዲሁም የእርባታ ቴክኖሎጂን በማስተዋወቅ ለአርሶና አርብቶ አደሩ ሕይወት ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋልም ነው ያሉት።
ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎቹም፥ ባለሀብቶቹ መንግስት ቅድሚያ በሚሰጣቸው ዘርፎች በአንዱ ላይ ለመስራት ላሳዩት ጥልቅ ፍላጎት አመስግነዋል።
አያይዘውም እንደ እነዚህ ያሉ እቅዶች በመካከለኛው ምስራቅ ካሉ ባህላዊ ገቢያዎች ውጭ ያሉትን ገቢያዎችን እንደሚያሰፉም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በአህጉሪቱ በእንስሳት ሀብት ቀዳሚ አገር ብትሆንም እስካሁን ከዘርፉ የተገኘው ውጤት በጣም ደካማ በመሆኑ እነዚህን ሰፊ ዕድሎች ለመጠቀም ብዙ መስራት ይገባልም ነው ያሉት።
የስጋ ማቀነባበሪያ ፋብሪካው ሥራ ሲጀምር በቀን 600 በሬዎች ፣ 5 ሺህ በጎች እና ፍየሎች እንዲሁም 100 ግመሎችን በመጀመሪያው ዙር የማምረት አቅም ይኖረዋል ተብሏል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
20,760
People Reached
879
Engagements
Boost Post
526
36 Comments
19 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.