Fana: At a Speed of Life!

ባለሀብቱ በሰሜን ሸዋ ዞን ለ2ሺህ ተማሪዎች ድጋፍ አደረጉ

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ሸዋ ዞን አጎላና ጠራ ወረዳ በላይነህ ደበበ የተባሉ ባለሀብት ለ2ሺህ ተማሪዎች የአንድ አመት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ ።

ባለሀብቱ በተለይም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት ÷ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ችግር እዳለባቸው ስለተነገረኝ በግብአት ችግር ምክንያት የሚያቋርጡ ተማሪዎች እዳይኖሩ ነው ከቤተሰቤ ጋር ይህን ድጋፍ ያደረኩት ብለዋል ።

በቀጣይም የሚጎድሉ የትምህርት ቁሳቁሶችን እናሟላለን ያሉት ባለሀብቱ መምህራን እና ወላጆች በጋራ ሀላፊነታቸውን በመወጣት ሀገር ተረካቢ የሆኑ ህፃናትን በተገቢ መንገድ ሊቀርፁ ይገባል ነው ያሉት ።

የተደረገው ድጋፍ በትምህርት ስርዓቱ ትልቅ ተግዳሮት የሆነውን የአቋራጭ ችግር የሚቀርፍ ነው ያሉት የአንጎላና ጠራ ወረዳ ትምህርት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አስፋው ዘዉዴ ተግባሩ ትልቅ አርዓያነት ያለው በመሆኑ መስፋት ያለበት ነዉ ሲሉ ተናግረዋል ።

ከ10ሺህ በላይ ደብተርና ስኪብርቶው አሁን ባለው ዋጋ ከ 300ሺህ ብር በላይ የሚገመት ነው ያሉት ሀላፊው ይህን ያገኙ ተማሪዎችም ወደትምህርት ቤት እዲመጡ መነሳሳት የፈጠረ ነው ብለዋል ።

የባለሀብቱ ድጋፍ የመማር ማስተማር ስራው ከመጀመሩ በፊት በምዝገባ ወቅት መምጣቱ ፋይዳው የጎላ ነው ያሉት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዮርዳኖስ ተከስተ ሌሎች ባለሀብቶችም ይህን አርዓያነት ያለው ተግባር በመፈፀም ለወገናቸው ሊደርሱ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል ።

በአበበ የሸዋልዑል

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.