Fana: At a Speed of Life!

1 ሺህ አንጀራ በመጋገር ለመከላከያ ሰራዊቱ ድጋፍ ያደረጉት የ80 ዓመት እናት

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በጎንደር ከተማ የሚኖሩ የ80 ዓመት እናት 1 ሺህ እንጀራ በመጋገር ለመከላከያ ሰራዊት ፣ ለአማራ ልዩ ሃይል ፣ሚሊሻ እና ፋኖ የስንቅ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ወይዘሮ ረህመት በሽር ሸንኮሬ የጎንደር ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ÷ የትህነግ የሽብር ቡድን ኢትዮጵያን አፈርሳላው ብሎ መነሳቱን ተክትሎ ሃገሬ ኢትዮጵያ አትፈርስም እኔ የ80 ዓመት አዛውንት ነኝ ጦር ሜዳ ገብቼ ባልዋጋም ለሰራዊቱ ደጀን እሆናለሁ ማለታቸው ተገልጿል፡፡

በዚህም 1ሺህ አንጀራ በመጋገር ፣50 ኪሎ ሽሮ በቤታቸው በማዘጋጀትና 100 ደርዘን ውሃ ለሰራዊቱ በማይጠብሪ ግንባር ድጋፍ ማድረጋቸውን ከጎንደር ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.