Fana: At a Speed of Life!

የትኛውንም የሀገር ውስጥና የውጭ ጥቃት ለመመከት ተዘጋጅተናል – የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞንና የወሊሶ ከተማ ወጣቶች አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የትኛውንም የሀገር ውስጥና የውጭ ጥቃት ለመመከት ተዘጋጅተናል ሲሉ የደቡብ

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የትኛውንም የሀገር ውስጥና የውጭ ጥቃት ለመመከት ተዘጋጅተናል ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞንና የወሊሶ ከተማ ወጣቶች ተናገሩ፡፡

ከዞን እና ከከተማ አስተዳደሩ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለሚቀላቀሉ ወጣቶች ሽኝት ተደርጓል።

በሽኝት ስነ ስርዓቱ ላይ የሀገር ሽማግሌዎች በድል እንዲመለሱ በማህበረሰው ባህል መሰረት ወጣቶቹን መርቀዋል።

የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መገርሳ ዲሪባ አባቶቻችሁ ሀገርን ከወራሪ በመጠበቅ ታሪክ እንደሰሩት ሁሉ እናተም ታሪክ ለመስራት ስለተዘጋጃችሁ ኮርተናል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ወጣቶቹ በበኩላቸው÷ ጀግናውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት በመቀላቀል የሀገር ውስጥ ከሀዲ እና የትኛውም የውጭ ጠላት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርገውን ደባ ለመመከት ተነስተናል ማለታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.