Fana: At a Speed of Life!

የምሁራን ማህበሩ ለደብረ ታቦር ሆስፒታል የአጥንት ሕክምና መሳሪያ አበረከተ

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ነዋሪነታቸው በአዲስ አበባ የሆኑ የእስቴ ወንድማማቾች ምሁራን ማኅበር አባላት ለደብረ ታቦር ሆስፒታል የአጥንት ሕክምና መሳሪያ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

በድጋፍ የተሰጠው የአጥንት ሕክምና መሳሪያ በሕልውና ዘመቻው ሆስፒታሉ የተጣለበትን ሃላፊነት እንዲወጣ ለማስቻል ነው ተብሏል፡፡

ድጋፉ በሆስፒታሉ የፍላጎት ጥያቄ መሰረት የተከናወነ መሆኑን መሳሪያውን ያስረከቡት ዶክተር መንግሥቱ እርቄ ገልጸዋል።

ዶክተር መንግሥቱ ለንፋስ መውጫ ሆስፒታልም ሌሎች የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል።

የደብረታቦር ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር አዲስ ደርበው የአጥንት ሕክምና መሳሪያው ውድ ዋጋ ያለው መሆኑ ብቻ ሳይሆን ቋሚ እቃ በመሆኑ ሆስፒታሉን ዘላቂ ተጠቃሚ እንደሚደርገው ጠቁመዋል፡፡

ውድመት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት መልሶ ለማቋቋምም ሌሎች ድጋፍ አድራጊዎች ያላሰለሰ ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ ማቅረባቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.