Fana: At a Speed of Life!

በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ የጦር መሳሪያ ተያዘ

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በህገ ወጥ መንገድ ከምዕራብ ጎንደር ዞን ወደ ጎንደር ከተማ ለመግባት ሲንቀሳቀስ የነበረ የጦር መሳሪያ መያዙ ተገለጸ።

የጦር መሳሪያው የተያዘው መነሻውን ምዕራብ ጎንደር ዞን አርማጭሆ ወረዳ በማድረግ ወደ ጎንደር ከተማ ለመግባት ሲንቀሳቀሰ ነው ።

የታርጋ ቁጥሩ ኮድ 3 አ/አ 17783 3F የሆነና እስማኤል ዳውድ በተባለ ግለሰብ ሲንቀሳቀስ በነበረ ተሽከርካሪ 82 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጦች፣ ከ20 ሺህ መሰል ጥይቶች እንዲሁም 2 ክላሽንኮቭ ጠመንጄዎች እና 50 መሰል ጥይቶች በድብቅ ለማጓጓዝ ሲሞክር ነዉ እጅ ከፈንጅ የተያዘዉ፡፡

ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ተጠርጣሪዉን ከመነሻው ጀምሮ ክትትል በማድረግ እና ሳንጃ የተባለዉ ኬላ ላይ ሲደርስ ጥቆማ በመስጠት በፀጥታ አካላት በቁጥጥር ስር እንዲውል መደረጉን አግልግሎቱ ገልጿል።

ዋና ተጠርጣሪውን ለመያዝ ክትትሉ ተጠናክሮ መቀጠሉንም አስታውቋል ፡፡

ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እንዲሁም ጉምሩክ እና የፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን በጋር እና በቅንጅት መሳተፋቸዉን ለመረጃዉ ቅርበት ያላቸዉ ምንጮቻችን አረጋግጠዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.