Fana: At a Speed of Life!

የወራሪው ቡድን ምርኮኞች የትግራይ እናቶች ልጆቻቸውን ወደ ጦርነት እንዳይልኩ ጠየቁ

 

አዲስ አበባ መስከረም 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቲሃ በኩል ሰርገው ገብተው የነበሩና በመከላከያ ሰራዊት የተማረኩ የጁንታው ቡድን ምርኮኞች የትግራይ እናቶች ልጆቻቸውን ወደ ጦርነት እንዳይልኩ ጠየቁ።

በሱዳን ወታደራዊ ስልጠና ወስደው በቲሃ በኩል ጦርነት በመክፈት ጎንደር ከተማን የመቆጣጠር ዓላማ እንደነበራቸው ነው ተማራኪ የአሸባሪው ቡድን አባላት የተናገሩት።

የወራሪውን ሃይል በመምራትና ከባድ መሳሪያዎችን በመተኮስ ጭምር ሲሳተፉ እንደነበር የገለጹት መጋቤ ሀምሳ አለቃ ብርሃ ወለደገብርኤልና ገብረመድህን ሀይሉ፥ በቲሃ በኩል በመከላከያ ሰራዊት ተማርከዋል።

“ ነፃ ትግራይን ለመፍጠር ተልዕኮ ተሰጥቶን ነው በሱዳን በኩል ወደ ጦርነት ተገደን የገባነው” የሚሉት እነዚሁ ምርኮኞች ምንም የማያውቁ የትግራይ ወጣቶች ፥ ለጦርነት እየተማገዱ መሆኑን ተናግረዋል።

ከዚህ በኋላ ዓላማ ለሌለው ጦርነት የትግራይ ህዝብ ልጆቹን ለጦርነት መላክ የለበትም የሚሉት ምርኮኞቹ ፤ ወጣቱ ከአሁን በኋላ የጁንታው መጠቀሚያ ከመሆን እንዲቆጠብ ጠይቀዋል።

የጁንታውን ትዕዛዝ ወደጎን በመተው የትግራይ ወጣት ራሱን ካልተፈለገ የጦርነት ኪሳራ ራሱን እንዲጠብቅም አሳስበዋል፡፡

በምናለ አየነው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.