Fana: At a Speed of Life!

የወንጌል አማኞች 300 ሺህ ብር የሚገመት የህፃናት ምግብ ለተፈናቃዮች አበረከቱ

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የሚኖሩ የወንጌል አማኞች 300 ሽ ብር የሚገመት የህፃናት ምግቦችን በደሴ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረጉ፡፡

በአዲስ አበባ የሚኖሩ የወንጌል አማኞች ለተፈናቃይ ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ በማሰብ ለህፃናት ምግብ የሚሆን ዱቄት፣ ሴሪፋም እና ፓስታ እንዲሁም ሳሙና በደሴ ከተማ በሚገኙ ተፈናቃዮች መለገሳቸውን አስተባባሪዋ ውቢት ግርማ ተናግረዋል፡፡

“ጋን በጠጠር ይደገፋል’ በሚል መርህ በዚህ ወቅት ይበልጥ ተጎጅ ለሆኑ ህፃናትና ሴቶች ያለንን ለመደጎም መጥተናል ብለዋል አስተባባሪዋ፡፡በቀጣይ ተመሳሳይ ድጋፍ እንደሚያደርጉም ገልፀዋል፡፡

የደሴ ከተማ ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ መምሪያ የጥናትና ፕሮጀክት ባለሙያ አቶ ሰለሞን ካሳ በበኩላቸው ድጋፉ ለ200 ህፃናት እንዲደርስ የተደረገ ሲሆን፣ ክፍፍሉ ፍትሀዊ እንዲሆንም በየክፍለ ከተማው እስከ 5 አመት የሆናቸው ከ2 ልጅ በላይ ያላቸው እና ይበልጥ ለችግር የተዳረጉትን የመለየት ስራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡

ተፈናቃዮችን የመደገፍ ተግባር በመንግስት አካል ብቻ የተሟላ ሊሆን አይችልም ያሉት አቶ ሰለሞን፥ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ግለሰቦች በቡድን በመሰባሰብ ለወገን ደራሽነታቸውን ማሳየት እንዳለባቸው ጠይቀዋል፡፡

የሰሜን ምስራቅ ክልል ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ህብረት የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ፓስተር ሰለሞን አበጋዝ ደግሞ የገጠመንን ችግር የምንሻገረው በጋራ ስንሆን ነው ብለዋል።

ከዚህ ቀደም በአብያተክርስቲያናቱ በኩል ከ120 ሽ ብር በላይ በሆነ ወጭ የተገዙ እቃዎችን ድጋፍ መደረጉን አስታውሰዋል፡፡

አሁን ደግሞ የወንጌል አማኞች በራሳቸው ተነሳሽነት እንደዚህ አይነት ድጋፍ ማድረጋቸው የሚመሰገን ተግባር ነው ብለዋል፡፡

ይከበር አለሙ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.