Fana: At a Speed of Life!

እኛ እያለን ኢትዮጵያ ነፃነቷ አይደፈርም – የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ወጣቶች

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከምስራቅ ሐረርጌ ዞን ተወጣጥተው የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለመቀላቀል ዝግጁ ለሆኑ ወጣቶች በሐረማያ ከተማ ሽኝት ተደርጎላቸዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የአፍሪካ መከታ መሆኑን የተናገሩት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሁሴን ፈይሶ፤ ወጣቶቹ ይህንን ሃይል ለመቀላቀል በመወሰናቸሁ ኩራት ሊሰማችሁ ይገባቸዋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ነፃነት በስንዴ ለመግዛት የሚፈልጉ አንዳንድ ሀገራት፣ ወጣቱ በቁርጠኝነት የሀገር መከላከያ ሠራዊትን በመቀላቀል ተገቢውን ምላሽ እየሰጣቸው እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

የሐረማያ ከተማ ከንቲባ አቶ ሙለታ ቡሽራ በበኩላቸው፣ ወጣቶቹ ሀገር ተነካች ብለው የሀገራቸውን ሉዓላዊነት ለማስከበርና ህዝባቸውን ከጥቃት ለመጠበቅ ላሳዩት ተነሳሽነት ኢትዮጵያ እንደምታመሰግናቸው ገልፀዋል።

እኛ እያለን ኢትዮጵያ ነፃነቷ አይደፈርም ያሉት ዘማቾቹ፣ ከሌሎች ወንድሞቻቸው ጋር በመሆን የጁንታውን ግብአተ መሬት እንደሚያፋጥኑት ገልፀዋል።

ከምስራቅ ሐረርጌ ዞን የተውጣጡ ወጣቶች፤ ከዚህ ቀደም በሁለት ዙሮች ጀግናውን የሀገር መከላከያ ሰራዊትን መቀላቀላቸው ይታወሳል።

በምንያህል መለሰ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.