Fana: At a Speed of Life!

2ኛ ዙር የብሔራዊ በጎ ፈቃደኞች አገልግሎት ሰልጣኞች ሁለገብ ድጋፍ አደረጉ

 

አዲስ አበባ መስከረም 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሊጂ ኢንስቲትዩት የሰላም ሚኒስቴር ያዘጋጀውን 2ኛ ዙር ሀገር አቀፍ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስልጠና እየወሰዱ የሚገኙ ወጣቶች ለመከላከያ ሠራዊት ደም ለገሱ፡፡

ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡት ወጣቶች ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ ሲሆን ለ45 ቀናት የኑሮ ክህሎት፣የሚዲያ ጠቀሜታ፣ ሲቪል ማህበረሰብ፣ ሰላም ግንባታ፣ሀገር ከወጣቶች ምን ትጠብቃለችና በሚሉ ርዕሶችና ሀገራዊ መግባባት ላይ ባተኮሩ ስልጠናዎችን ተሳታፊ የሆኑ ናቸው፡፡

ከሚሰጣቸው ስልጠና ጎን ለጎን በራሳቸው ተነሳሽነት የተለያዩ የበጎ ፈቃድ ስራዎች ላይ መሰማራታቸውን የገለፁት ወጣቶቹ መስከረም 1/ 2014 ዓ.ም አዲስ ዓመት ላይ ሁሉም ምሳቸውን በመተው ከ200 በላይ አቅመ-ደካሞችን የመገቡ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለት ደገሞ ከ100 በላይ ሰልጣኞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ደም ለግሰዋል፡፡

የተለያዩ አልባሳትን ና የትምህርት ቁሳቁሶችን እያሰባሰቡም ሲሆኑ በቀጣይ በከተማ ፅዳት ተግባር ላይ እንደሚሰማሩም ገልፀዋል፡፡

በጅማ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሊጂ ኢንስቲትዩት የ2 ኛ ዙር የሰላም ሚኒስቴር ብሔራዊ በጎ ፈቃደኛ ማህበረሰብ ልማት አገልግሎት ወጣት ሰልጣኞች አስተባባሪ ወ/ሮ ትዕግስት ኃይለማሪያ ከዚህ ቀደም በአካባቢያቸው ብቻ ታጥሮው የነበሩት ወጣት ሰልጣኞች ከ45 ቀናት ስልጠና በኃላ ከመጡበት ክልል ውጭ ወደ ማያውቁት ሀገሪቱ አካባቢ በመሄድ ለ10 ወር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንደሚሰጡ ተናግረዋል፡፡

ወጣቱን ያላሳተፈ ሀገራዊ ዕድገት ስለማይኖር ወጣቱን በማህበራዊ ልማት ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ ጠቀሜታው ብዙ ነው ብለዋል፡፡

ወጣቶቹ “በጎነት ለአብሮነት “ በሚል መርህ በተለያዩ የበጎ ፈቃድ ተግባራት ላይ መሳተፋቸው በቀጣይ የመረዳዳትና መተጋገዝ ባህል እንዲዳብር ያደርጋልም ነው ያሉት፡፡

2ኛውን ዙር ስልጠና ከ5 ሺህ 600 በላይ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ ወጣቶች እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡

በተመስገን አለባቸው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.