Fana: At a Speed of Life!

የጅማ ዩኒቨርሲቲ በወሎ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የ2.45 ሚሊየን ብር የአይነት ድጋፍ አደረገ

 

አዲስ አበባ መስከረም 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅማ ዩኒቨርሲቲ በወሎ ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች 2 ነጥብ 45 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የአይነት ድጋፍ አደረገ።

ዩኒቨርሲቲው በወሎ ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች የምግብ ዘይት፣ ፍራሽ ፣ ብርድ ልብስ፣ ሩዝ፣ በርበሬና ሽሮ እንዲሁም ልዩ ልዩ የመመገቢያ እቃዎችን ያካተተ ድጋፍ ኘው ያደረገው።

ለተፈናቃይ ወገኖች የተደረገው ድጋፍ በወሎ ዩኒቨርሲቲ በኩል የሚሰጥ መሆኑን የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዛዳንት ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ ተናግረዋል ፡፡

ዶር ቀነኒሳ አክለውም አገራችን የገጠማትን ፈተና ለመቋቋም በጋራ መቆም እንዳለብንና ይህ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ለተፈቃናዮች የተደረገ ድጋፍም የዚሁ አካል ነው ብለዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው “ለወገን ደራሽ ወገን ነው” በሚል መርህ፣ ከአሁን በፊት ለአማራ ክልል በደባርቅና ደብረ ታቦር ለሚገኙ ወገኖች 3 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር፣ ከዚህ ውስጥ 2 ነጥብ 1 ሚሊየን ብሩ ለደባርቅ ሆስፒታል የሚውል የህክምና መገለልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን የጅማ የኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ገልፀዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በሰመራ ዩኒቨርሲቲ በኩል የተከፋፈለ 2 ነጥብ 4 ሚሊየን በር የሚገመት ድጋፍ የተደረገ ሲሆን፣ የዛሬውን ጨምሮ በተከታታይ የጅማ ዩኒቨርሲቲ የ7.95 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የምግብ፣ አልባሳት፣ የህክምና መገልገያ ቁሳቁስና የመመገቢያ እቃዎች ድጋፍ ማድረጉን ዶ/ር ጀማል አስታውቀዋል፡፡

ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ፣ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚውል፣ በጠቅላላው የ32 ነጥብ 03 ሚሊየን ብር ድጋፍ መደረጉን ከዩኒቨርስቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.