Fana: At a Speed of Life!

የምስራቅ ጎጃም ዞን10 ሺህ ተማሪዎች በነፃ ለማስተማር ወሰነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር አሸባሪው ትህነግ ከትምህርት ገበታ እንዲነጠሉ የወሰነባቸዉ 10ሺህ ተማሪዎች በነፃ ለማስተማር ወሰነ።

የትህነግ አሸባሪ ሃይል በፈጸመው ወረራና ጅምላ ጭፍጨፋ የጦርነቱ ሰለባ የሆኑ ተማሪዎችን በምስራቅ ጎጃም ዞን በሚገኙ ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች ተቀብሎ ለአንድ ዓመት በነፃ ለማስተማር ወስኗል።

የምስራቅ ጎጃም ዞን  ዋና  አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አያሌዉ እንደገለጹት፥ አሸባሪው ቡድን በሰው ልጅ ህይወት ላይ ከፈጸመው አሰቃቂ እልቂት፣ በተቋማት ላይ  ባደረሰው ውድመት  ህጻናትን ያላሳዳጊና ከትምህርት ገበታ ዉጭ አድርጓል እንዲሆኑ አድርጓል ብለዋል።

የምስራቅ ጎጃም ዞን ህዝብ ጠላት በአማራነቱ የጥቃት ሰለባ ያደረገዉን የወሎን ህዝብ አጋርነቱን ለማሳየት በዞኑ ዉስጥ የሚገኙ 26 የገጠርና የከተሞች አስተዳደሮች 10ሽ የችግሩ ሰለባ የሆኑ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለአንድ ዓመት ለማስተማር ወስኗል።

የዞን አስተዳደሩ ተማሪዎችን ተቀብሎ በነፃ ለማስተማር የወሰነው ከ5ኛ  እስከ  12ኛ ክፍል ደረጃ የሚገኙ ተማሪዎችን እንደሆነም ዋና አስተዳዳሪ ተናግረዋል።

የመምረጫ መመዘኛውም ወራሪው ቡድን በፈጸመው ግፍ ምክንያት ወላጆቻቸውን በሞት ያጡና ትምህርት ቤታቸው የፈረሰባቸውና ወላጆቻቸው ሌላ ቦታ ልከዉ ለማስተማር አቅም የሌላቸዉ  ህፃናት ተማሪዎችን እንደሆነም አስተዳዳሪው አብራርተዋል።

ተማሪዎቹ ተመርጠው እንዲላኩላቸውም በነገዉ እለት ለአማራ ክልል ትምህርት ቢሮና ለሰሜን ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ በድብዳቤ እንደሚጠይቁም አቶ አብርሃም ተናግረዋል ።

ይህ ዉሳኔ የተወሰነዉ የዞንና የወረዳ አመራሮች ወቅታዊ የስራ አፈፃፀሞች  ዙሪያ በደብረማርቆስ ከተማ ዉይይት ካደረጉ በኋላ መሆኑን ከአማራ ኮሚዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.