Fana: At a Speed of Life!

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አመራርና ሰራተኞች 9 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አመራርና ሰራተኞች 9 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

በርክክብ ስነ ስርዓቱ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው እንዳሉት÷ ተቋሙ የህዝብ ሚዲያ መሆኑን ለማረጋገጥ ልማትን በማገዝና የህዝብ ፍላጎቶችን በማስጠበቅ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል።

ፋና በመረጃ ብቻ ሳይሆን በህዝቡ ሰላምና ደህንነት ሀዘንና ደስታ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ስራ አስፈፃሚው አውስተውዋል፡፡

የፋና አመራርና ሰራተኞችም ከጀግናው መከላከያ ሰራዊቱ ጎን በመሆን የአንድ ወር ደመወዛቸውን መስጠታቸውን ተናግረዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የመከላከያ ፋይናንስ መምሪያ ሀላፊ ብርጋዴር ጀኔራል ዓለምሰገድ ወንድወሰን ÷ፋና በመከላከያ ውሎዎች እየዋለ ገድሉን የሚዘግብ ጀግና ሚዲያ ነው ብለዋል።

 

ጠላት የሚያሰራጨውን የሀሰት ፕሮፖጋንዳ በመመከትም ሙያዊ እገዛ አድርጓል ነው ያሉት።

በአፈወርቅ እያዩ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.